Our Statement of Faith

Maryland Kaleheywet Church Statement of Faith

We believe in God who is self-existent, eternal, all-knowing, all-powerful, creator of the universe and the human beings, and present everywhere. God has eternally existed in three co-equal persons: God the Father, God the Son (Jesus), and God the Holy Spirit. (Matthew 28:19-20; 2 Corinthians 13:14). The Father, Son, and Holy Spirit are in agreement and unified with each other as the Godhead. We believe these three persons are co-equal and are one God. (Genesis 1:1, 26-27; 3:22; Deuteronomy 6:4; Job 38, 39, & 40; Psalm 90:2, 139:1-4, 7-10; Isaiah 40:13-17,45; 1 Peter 1:2; John 1:1, Colossians 1:15; Revelation 4:11).

Amharic version

እግዚአብሔር አብ

በራሱ የሚኖር፣ የዘላለም፣ ሁሉን አዋቂ፣ ሁሉን ቻይ፣ የጽንፈ ዓለምና የሰው ልጆች ፈጣሪ፣ እንዲሁም በሁሉም ቦታ በሚገኝ በእግዚአብሔር እናምናለን። እግዚአብሔር ለዘላለም እኩል በሆኑ በሦስት አካላት ይኖራል፤ እነርሱም፦ እግዚአብሔር አብ፣ እግዚአብሔር ወልድ (ኢየሱስ) እና እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ናቸው (ማቴዎስ 28:19-20፤ 2 ቆሮንቶስ 13:14)። አብ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ በመለኮትነት አንድነትና ስምምነት ያላቸው ናቸው። እነዚህ ሦስት አካላት እኩል እንደሆኑና አንድ አምላክ እንደሆኑ እናምናለን (ዘፍጥረት 1:1, 26-27፤ 3:22፤ ዘዳግም 6:4፤ ኢዮብ 38, 39, እና 40፤ መዝሙረ ዳዊት 90:2, 139:1-4, 7-10፤ ኢሳይያስ 40:13-17, 45፤ 1 ጴጥሮስ 1:2፤ ዮሐንስ 1:1, ቆላስይስ 1:15፤ ራእይ 4:11)።

We believe that Jesus Christ is the Son of God and He is God who was born of the Virgin Mary, fully God and fully human. Jesus is coequal with the Father and the Holy Spirit, and present and participating in creation. Jesus took on human flesh in the fullness of time so that He could live a sinless life and offer Himself as the perfect sacrifice for the sins of all people by dying on the cross. He was raised from the dead on the third day, victorious over the power of sin and death. He ascended to heaven and is seated at the right hand of the Father. He will come again to judge the living and the dead and to make all things new. We believe that the only means of being cleansed from sin is through repentance and faith in Jesus Christ, and that Jesus Christ is the only Mediator between God and human beings. (John 1:1; Philippians 2:6; John 14:9; Isaiah 7:12; Luke 1:30; Hebrew 4:6; 1 Corinthians 15:3-8; 1 Timothy 2:5; 3:16; Romans 3:24-25; Mark 16:19; Acts 1:9, 11, 10-42; Revelation 1:7-20; 22:12; 1 Thessalonians 2:16, 4:15-17; John 1:10)

 

Amharic version

ኢየሱስ ክርስቶስ

ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነና ከድንግል ማርያም የተወለደ፣ ፍጹም አምላክና ፍጹም ሰው የሆነ አምላክ እንደሆነ እናምናለን። ኢየሱስ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እኩል የሆነ፣ በፈጠራም ወቅት የነበረና የተሳተፈ ነው። ኃጢአት የሌለበትን ሕይወት እንዲኖርና በመስቀል ላይ በመሞት ለሰው ልጆች ሁሉ ኃጢአት ፍጹም መሥዋዕት አድርጎ ራሱን እንዲያቀርብ፣ በዘመኑ ፍጻሜ የሰውን ሥጋ ለበሰ። በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተነሳ፤ በኃጢአትና በሞት ኃይል ላይም ድልን ተቀዳጀ። ወደ ሰማይ ዐረገ፤ በአብ ቀኝም ተቀመጠ። በሕያዋንና በሙታን ላይ ለመፍረድና ሁሉንም ነገር አዲስ ለማድረግ ዳግመኛ ይመጣል። ከኃጢአት የመንጻት ብቸኛው መንገድ ንስሐ መግባትና በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን እንደሆነ፣ እንዲሁም ኢየሱስ ክርስቶስ በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ብቸኛው መካከለኛ እንደሆነ እናምናለን (ዮሐንስ 1:1፤ ፊልጵስዩስ 2:6፤ ዮሐንስ 14:9፤ ኢሳይያስ 7:12፤ ሉቃስ 1:30፤ ዕብራውያን 4:6፤ 1 ቆሮንቶስ 15:3-8፤ 1 ጢሞቴዎስ 2:5፤ 3:16፤ ሮሜ 3:24-25፤ ማርቆስ 16:19፤ የሐዋርያት ሥራ 1:9፣ 11፣ 10-42፤ ራእይ 1:7-20፤ 22:12፤ 1 ተሰሎንቄ 2:16፣ 4:15-17፤ ዮሐንስ 1:10)።

We believe that the Holy Spirit is God, who is a co-Creator with the Father and Son, sent by the Father through the Son to convict the world of sin. The Holy Spirit is a comforter who leads us into all truth, and empower and equip the Church to carry on Christ’s work on earth. The Holy Spirit dwells in every Christian from the moment of salvation, and He distributes spiritual gifts, and He convicts the world concerning sin, righteousness and judgment. (Genesis 1:2; John 14:26; 15:26; 16:8; 2 Peter 1:21; Acts 1:8; 1Coranthians 12:4-11; Ephesians 1:13; 4:11-12).

 

Amharic version

መንፈስ ቅዱስ

መንፈስ ቅዱስ ከአብና ከወልድ ጋር ዓለምን በመፍጠር የተሳተፈ አምላክ እንደሆነ፣ እንዲሁም ዓለምን ስለ ኃጢአት እንዲወቅስ በአብ አማካኝነት በወልድ በኩል የተላከ እንደሆነ እናምናለን። መንፈስ ቅዱስ ወደ እውነት ሁሉ የሚመራን አጽናኝ፣ እንዲሁም የክርስቶስን ሥራ በምድር ላይ እንድትቀጥል ቤተክርስቲያንን የሚያስታጥቅና ኃይል የሚሰጥ ነው። መንፈስ ቅዱስ ከደህንነት ቅጽበት ጀምሮ በእያንዳንዱ ክርስቲያን ውስጥ ይኖራል፤ መንፈሳዊ ስጦታዎችንም ያድላል፤ እንዲሁም ዓለምን ስለ ኃጢአት፣ ስለ ጽድቅና ስለ ፍርድ ይወቅሳል (ዘፍጥረት 1:2፤ ዮሐንስ 14:26፤ 15:26፤ 16:8፤ 2 ጴጥሮስ 1:21፤ የሐዋርያት ሥራ 1:8፤ 1 ቆሮንቶስ 12:4-11፤ ኤፌሶን 1:13፤ 4:11-12)።

We believe that the Bible, both the Old and the New Testament, is the Word of God. The Bible has a human and divine authors where they wrote under the supernatural guidance of the Holy Spirit. Because it is inspired by God, the Bible is infallible, inerrant, and absolute truth. It is the ultimate and final authority for Christian beliefs and living (Psalms 12:6; 119:105; Proverbs 30:5; 2 Timothy 1:13, 3:16; 2 Peter 1:20-21; Romans 15:4; 1 Corinthians 10:11; 1 Thessalonians 2:13).

 

Amharic version

መጽሐፍ ቅዱስ

ብሉይ ኪዳንም ሆነ አዲስ ኪዳንን ያካተተው መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል እንደሆነ እናምናለን። መጽሐፍ ቅዱስ በመንፈስ ቅዱስ መለኮታዊ መሪነት የተጻፈ ሲሆን፣ ሰዋዊና መለኮታዊ ደራስያን አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ በእግዚአብሔር መንፈስ መሪነት የተጻፈ በመሆኑ የማይሳሳት፣ ስህተት የሌለበትና ፍጹም እውነት ነው። ለክርስቲያናዊ እምነትና አኗኗርም የመጨረሻውና የበላይ ሥልጣን ነው (መዝሙረ ዳዊት 12:6፤ 119:105፤ ምሳሌ 30:5፤ 2 ጢሞቴዎስ 1:13፣ 3:16፤ 2 ጴጥሮስ 1:20-21፤ ሮሜ 15:4፤ 1 ቆሮንቶስ 10:11፤ 1 ተሰሎንቄ 2:13)።

We believe that all have sinned and fell short of the glory of God. The wages of sin is death and eternal separation from God. Salvation is a free gift of God. Jesus Christ’s death and his resurrection is the only sufficient payment for our sins. It’s only by grace through faith that one can receive this free gift. Eternal life begins the moment one receives Jesus Christ as Lord and Savior of their life. This is evidenced by repentance, confession, baptism by immersion, and a life submitted to Christ (Matthew 1:21; Luke 1:68-69; John 1:12, 14:6; Romans 3:23; 5:1, 6:23;10:9-13; Galatians 3:26; Ephesians 2:8-9; Titus 3:5; Acts 2:38-40).

 

Amharic version

ደህንነት

ሰው ሁሉ ኃጢአትን እንደሠራና የእግዚአብሔርም ክብር እንደጎደለው እናምናለን። የኃጢአት ደመወዝ ሞትና ለዘላለም ከእግዚአብሔር መለየት ነው። ደህንነት የእግዚአብሔር ነፃ ስጦታ ነው። ለኃጢአታችን ብቁ የሆነው ብቸኛው ክፍያ የኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ነው። ይህን ነፃ ስጦታ መቀበል የሚቻለው በጸጋ፣ በእምነት በኩል ብቻ ነው። የዘላለም ሕይወት የሚጀምረው አንድ ሰው ኢየሱስ ክርስቶስን የሕይወቱ ጌታና መድኃኒት አድርጎ ከተቀበለበት ቅጽበት ጀምሮ ነው። ይህም በንስሐ፣ በኑዛዜ፣ በውኃ በመጥለቅ በሚደረግ ጥምቀትና ለክርስቶስ በተገዛ ሕይወት ይረጋገጣል (ማቴዎስ 1:21፤ ሉቃስ 1:68-69፤ ዮሐንስ 1:12፣ 14:6፤ ሮሜ 3:23፤ 5:1፣ 6:23፤ 10:9-13፤ ገላትያ 3:26፤ ኤፌሶን 2:8-9፤ ቲቶ 3:5፤ የሐዋርያት ሥራ 2:38-40)።

We believe that the Church is the gathering of believers who have come to faith in Jesus Christ as their Savior and Lord and who have been baptized by the Holy Spirit and became one body at the moment of their conversion. The main mission of the church is the Great Commission, to preach the gospel and to make disciples of Jesus. We believe that the Lord Jesus is the head of the Church (Matthew 16:18; Acts 2:41; 15:13-17; Ephesians 1:3-6; 1 Corinthians 12:12-13).

 

Amharic version

ቤተክርስቲያን

ቤተክርስቲያን በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነትና ጌታነት አምነው የተሰበሰቡ አማኞች ስብስብ እንደሆነች፣ እንዲሁም በንስሐ ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ ተጠምቀው አንድ አካል የሆኑ አማኞች አንድነት እንደሆነች እናምናለን። የቤተክርስቲያን ዋና ተልዕኮ ወንጌልን በመስበክና የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት በማድረግ የተሰጠውን ታላቁን ተልዕኮ መፈጸም ነው። ጌታ ኢየሱስ የቤተክርስቲያን ራስ እንደሆነ እናምናለን (ማቴዎስ 16:18፤ የሐዋርያት ሥራ 2:41፤ 15:13-17፤ ኤፌሶን 1:3-6፤ 1 ቆሮንቶስ 12:12-13)።

We believe that baptism is a public declaration of one’s faith in Jesus Christ and a commitment to follow him. All believers who accepted Jesus Christ as their personal savior would be baptized in obedience to Jesus’ commandments. We believe that the Christian baptism by immersion in water in the name of the Father, the Son, and the Holy Spirit (Mathew 28:19-20; Mark 16:16; Acts 10:47-48; Romans 6:1-4).

 

Amharic version

የውኃ ጥምቀት

ጥምቀት አንድ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያለውን እምነትና እርሱን ለመከተል የገባውን ቃል በይፋ የሚገልጽበት እንደሆነ እናምናለን። ኢየሱስ ክርስቶስን የግል አዳኛቸው አድርገው የተቀበሉ አማኞች ሁሉ ለጌታ ትእዛዝ በመታዘዝ ይጠመቃሉ። ክርስቲያናዊ ጥምቀት በአብ፣ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም በውኃ ውስጥ በመጥለቅ እንደሚፈጸም እናምናለን (ማቴዎስ 28:19-20፤ ማርቆስ 16:16፤ የሐዋርያት ሥራ 10:47-48፤ ሮሜ 6:1-4)።

We believe that Christians are called to glorify the Lord by obeying the word of God and living a holy and fruitful life. (James 1:22-25; Luke 8:8-15; 2 Timothy 2:19; Hebrews 12:14; 1 Peter 1:15-16; Galatians 5:22-24; 1 John 2:6)

 

 

Amharic version

ቅድስና

ክርስቲያኖች የእግዚአብሔርን ቃል በመታዘዝ እንዲሁም ቅዱስና ፍሬያማ ሕይወትን በመኖር ጌታን እንዲያከብሩ የተጠሩ መሆናቸውን እናምናለን (ያዕቆብ 1:22-25፤ ሉቃስ 8:8-15፤ 2 ጢሞቴዎስ 2:19፤ ዕብራውያን 12:14፤ 1 ጴጥሮስ 1:15-16፤ ገላትያ 5:22-24፤ 1 ዮሐንስ 2:6)።

We believe that marriage is a holy union between one man (by birth) and one woman (by birth). We believe that marriage is a holy institution created by God in the Garden of Eden. It is a covenant between a man and a woman to be together until death. (Genesis 2:18, 21-24; Ephesians 5: 21-33; Matthew 19: 3-9; Hebrew 13:4).

 

Amharic version

ጋብቻ

ጋብቻ በአንድ ወንድ (በተፈጥሮ/በልደት) እና በአንዲት ሴት (በተፈጥሮ/በልደት) መካከል የሚደረግ ቅዱስ አንድነት እንደሆነ እናምናለን። ጋብቻ በኤደን ገነት በእግዚአብሔር የተመሰረተ ቅዱስ ሥርዓት እንደሆነ እናምናለን። ይህም በአንድ ወንድና በአንዲት ሴት መካከል እስከ ሞት ድረስ አብሮ ለመኖር የሚደረግ ቃል ኪዳን ነው (ዘፍጥረት 2:18፣ 21-24፤ ኤፌሶን 5:21-33፤ ማቴዎስ 19:3-9፤ ዕብራውያን 13:4)።

We believe that our Lord Jesus Christ who ascended into heaven to the right-hand side of God the Father will return from heaven to earth. Jesus’ second coming will be personal, visible, and glorious. When he returns both the living shall be transformed and the dead in Christ shall be resurrected for judgment. All believers will live in a new heaven and a new earth with him forever. Those who did not obey God and did not believe in Jesus will be judged and cast into the lake of fire for everlasting punishment which is called the second death (Mathew 25:34-46; Luke 12:40; Acts 1:9-11; Titus 2:13; Hebrews 9:27; Revelation 20:10-15, 19:11-14).

 

Amharic version

የክርስቶስ ዳግም ምጽዓት

ወደ ሰማይ ዐርጎ በእግዚአብሔር አብ ቀኝ የተቀመጠው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማይ ወደ ምድር እንደሚመለስ እናምናለን። የኢየሱስ ዳግም ምጽዓት አካላዊ፣ ግልጽና በክብር ይሆናል። እርሱ በሚመለስበት ጊዜ በሕይወት ያሉቱ ይለወጣሉ፣ በክርስቶስ ያንቀላፉትም (የሞቱትም) ለፍርድ ይነሳሉ። አማኞች ሁሉ ከአርሱ ጋር በአዲስ ሰማይና በአዲስ ምድር ለዘላለም ይኖራሉ። ለእግዚአብሔር ያልታዘዙና በኢየሱስ ያላመኑ ግን ይፈረድባቸዋል፤ እንዲሁም ሁለተኛ ሞት ወደተባለው የዘላለም ቅጣት ወደ እሳት ባሕር ይጣላሉ (ማቴዎስ 25:34-46፤ ሉቃስ 12:40፤ የሐዋርያት ሥራ 1:9-11፤ ቲቶ 2:13፤ ዕብራውያን 9:27፤ ራእይ 20:10-15፣ 19:11-14)።