Our Evangelism Group exists to make Jesus known—boldly, lovingly, and consistently. We are a committed team that coordinates and strengthens all evangelism ministries in the church, creating pathways for the gospel to reach our neighborhoods and beyond.
Through regular outreach events, prayer gatherings, evangelism trainings and conferences, and the preparation of tracts and gospel resources, we equip believers to share Christ with wisdom, compassion, and confidence. We also provide practical support and organization so outreach is not occasional, but a steady rhythm of mission.
Under this ministry, we are grateful for our Evangelism Partners—faithful supporters who pray continually and contribute financially to sustain mission work over time. Whether you feel called to go, to serve, to pray, or to give, there is a place for you. Join us as we plant seeds, serve people, and trust God for a harvest.
የወንጌል ስርጭት ቡድን
የቤተክርስቲያናችን የወንጌል ስርጭት ቡድን ዋና ዓላማ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በድፍረት፣ በፍቅር እና ሳያቋርጥ ለዓለም ማሳወቅ ነው። በቤተክርስቲያናችን ሁሉንም የወንጌል አገልግሎቶች የሚያስተባብርና የሚያጠናክር የተሰጠ ቡድን ስላለን ስለእነርሱ እግዚኣብሔርን እናመሰግናለን። እንርሱ በዋናነት የምስራቹ ቃል እስከ ጎረቤቶቻችን አልፎም እስከ ዓለም ዳርቻ የሚደርስበትን መንገድ በመቀየስ ከቤተክርስቲያናችን መሪዎች ጋር ኣብረዉ ይሰራሉ።
አማኞች ክርስቶስን በጥበብ፣ በርኅራኄና በልበ-ሙሉነት እንዲመሰክሩ ለማስታጠቅ የሚከተሉትን ተግባራት እናከናውናለን፦
አገልግሎታችን አልፎ አልፎ የሚደረግ ክንውን ሳይሆን፣ ዘላቂ የሆኑ የተልዕኮ ጉዞዎች እንዲኖሩን ተግባራዊ ድጋፎችንና ስልታዊ ቅንጅቶችን እናቀርባለን።
በዚህ አገልግሎት ሥር፣ በጸሎታቸው የማይለዩንና የተልዕኮ ሥራው ቀጣይነት እንዲኖረው በገንዘባቸው ለሚደግፉን የወንጌል አጋሮቻችን ትልቅ ምስጋና አለን። ለመሄድ፣ ለማገልገል፣ ለመጸለይ ወይም ለመስጠት በልብዎ ጥሪ ካለዎት፤ እዚህ ለእርስዎ የሚሆን ስፍራ አለና ያግኙን። ዘርን እየዘራን፣ ሰዎችን እያገለገልንና ለእርሻውም ምርት እግዚአብሔርን እየተማመንን አብረን እንስራ።