በሰሜን አሜሪካ የሜሪላንድ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን እንኳን ደህና መጡ
በሰሜን አሜሪካ የሜሪላንድ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ስም ወደ ድረ-ገጻችን በታላቅ ደስታና ፍቅር እንኳን ደህና መጡ እንላለን!
ይህ መድረክ እርስ በርሳችን የምንገናኝበት፣ የክርስቶስን ፍቅር የምናካፍልበት እንዲሁም ሌሎችን በእምነትና በኅብረት ጉዟችን እንዲቀላቀሉን የምንጋብዝበት አንዱ መንገድ ነው።
ቅዱስ ቃሉ በዕብራውያን 10፡24–25 ላይ እንዲህ በማለት እንደሚያሳስበን፦ “ለፍቅርና ለመልካምም ሥራ እንድንነቃቃ እርስ በርሳችን እንተያይ፤ አንዳንዶችም እንደሚያደርጉት መሰብሰባችንን አንተው፤ ይልቁንም ቀኑ ሲቀርብ እያያችሁ አብልጣችሁ እርስ በርሳችን እንመካከር።”
ምኞታችን ይህንን ጥሪ በተግባር የምንኖር መሆንና የላቀ የእምነት ቤተሰብ መሆን ነው — እርስ በርስ ደግሞ የምንነቃቃበት፣ የምንታነጽበት እንዲሁም በኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅርና እውነት አብረን የምንጓዝበት የማኅበረሰብ መንፈሳዊ ጉዞ ነዉ።
Welcome to Maryland Kale Hiwot Church of North America
We warmly and joyfully welcome you, in the name of Maryland Kale Hiwot Church of North America, to our website with great love and gladness!
This platform is one of the ways we connect with one another, share the love of Christ, and invite others to join us in our journey of faith and fellowship.
As the Holy Scripture reminds us in Hebrews 10:24–25:
“And let us consider one another in order to stir up love and good works, not forsaking the assembling of ourselves together, as is the manner of some, but encouraging one another—and all the more as you see the Day approaching.”
Our desire is to live out this calling in practice and to become a strong family of faith — a community where we encourage one another, build each other up, and walk together in the love and truth of Jesus Christ.
Our Identity and Purpose
We are a Christ-centered, Bible-based, Spirit-led church family.
We exist to glorify God, build up believers, and reach out to the lost with the transforming message of Jesus Christ.
We believe the Church is not merely a building, but a living body — a people united by faith, love, and purpose.
God has been working in amazing ways through our church to proclaim the Gospel both locally and globally. We are deeply aware that to whom much is given, much is required. We have inherited a legacy of faith and mission from our pioneer leaders, and we are committed to carrying that legacy forward — to proclaim Christ, to plant churches, and to make disciples wherever God sends us.
We do not seek to mirror the comfort of the “American Dream,” but rather to live out God’s dream — to be light and salt in this world, living lives that make an eternal difference in both word and deed.
Our Commitment
Now is our time to shine the light of the Gospel with passion and compassion.
Let us pray together, encourage one another, and engage wholeheartedly in fulfilling the Great Commission of Jesus Christ — here in North America and beyond.
Together, may we continue to be a church that reflects the love of Christ, transforms lives, and impacts generations to come.
Welcome once again — we’re so glad you’re here!
ራእያችንና ጥሪያችን
ራእያችን የጌታን ታላቅ ተልዕኮ (ማቴዎስ 28፡18–20) በመታዘዝ፤ በአብ፣ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቅን፣ እያስተማርንና እየሰበክን የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ማስፋፋትና አሕዛብን ሁሉ ደቀ መዛሙርት ማድረግ ነው።
ይህ ራእይ በሰሜን አሜሪካ ምድር መልክ መያዝ የጀመረው የሜሪላንድ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ከተመሰረተችበት ጊዜ ጀምሮ ነው። እ.ኤ.አ. በመጋቢት 2015 በሁለት ቤተሰቦች (በአምስት ሰዎች) በአንድ ቤት ውስጥ በትንሽ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትና የጸሎት ኅብረት የተጀመረው አገልግሎት፣ በእግዚአብሔር ጸጋ በፍጥነት አደገ። በአምስት ወራት ውስጥ በሐምሌ 2015 የKHCNA ጉባኤን ያስተናገድን ሲሆን፣ በዚያው ዓመት በኅዳር 2015 የሜሪላንድ ቃለ ሕይወት ኅብረት በይፋ ተመስርቶ ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትና የጸሎት ፕሮግራሙን ቀጠለ።
በሚያዝያ 2016 የሜሪላንድ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን በአሜሪካ ሕጋዊ እውቅና አገኘች፤ ይህም ለእግዚአብሔር ታማኝነትና ለሕዝቡ ጽኑ ጸሎት ሕያው ምስክር ነው።
ማንነታችንና ዓላማችን
እኛ በክርስቶስ ማዕከልነት የምንመራ፣ በመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ላይ የቆምንና በመንፈስ ቅዱስ የምንመራ የቤተ ክርስቲያን ቤተሰብ ነን።
የምንኖረው እግዚአብሔርን ለማክበር፣ አማኞችን ለማነጽና በኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወት ለዋጭ ወንጌል የጠፉትን ለመፈለግ ነው። ቤተ ክርስቲያን ሕንጻ ብቻ ሳትሆን ሕያው አካል መሆኗን እናምናለን — ይህም በእምነት፣ በፍቅርና በዓላማ የተሳሰረ ሕዝብ ነው።
እግዚአብሔር በአጥቢያችንም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ወንጌልን ለማወጅ በቤተ ክርስቲያናችን በኩል በሚያስደንቅ ሁኔታ እየሠራ ይገኛል። “ብዙ ከተሰጠው ሁሉ ብዙ ይፈለግበታል” የሚለውን ቃል በጥልቀት እንረዳለን። ከቀደሙት መሪዎቻችን የእምነትና የተልዕኮ ቅርስን ወርሰናል፤ ያንንም ቅርስ ወደፊት ለማስቀጠል — ክርስቶስን ለመስበክ፣ አብያተ ክርስቲያናትን ለመትከልና እግዚአብሔር በሚልከን ስፍራ ሁሉ ደቀ መዛሙርትን ለማፍራት ቆርጠናል።
ፍላጎታችን “የአሜሪካን ሕልም” (American Dream) ምቾት መከተል ሳይሆን፣ የእግዚአብሔርን ሕልም መኖር ነው — በዚህ ዓለም ላይ ጨውና ብርሃን በመሆን፣ በቃልም ሆነ በተግባር ለዘላለም የሚተርፍ ለውጥ ማምጣት ነው።
ቃል ኪዳናችን
አሁን በታላቅ ቅንዓትና በፍቅር የወንጌልን ብርሃን የምናበራበት ጊዜ ነው።
በአንድነት እንጸልይ፣ እርስ በርሳችን እንበረታታ፣ እንዲሁም እዚህ በሰሜን አሜሪካና ከዚያም ባለፈ የኢየሱስ ክርስቶስን ታላቅ ተልዕኮ ለመፈጸም በሙሉ ልባችን እንትጋ።
በጋራ በመሆን የክርስቶስን ፍቅር የምታንጸባርቅ፣ ሕይወትን የምትለውጥና ለሚመጡት ትውልዶች ተጽዕኖ የምታሳርፍ ቤተ ክርስቲያን ሆነን እንቀጥል።
ደግመን እንኳን ደህና መጡ እንላለን — አብራችሁን በመሆናችሁ እጅግ ደስ ብሎናል!