Prayer is the heartbeat of our church. While prayer involves the whole congregation, we also have a dedicated Prayer Group that helps coordinate and strengthen our church-wide prayer lives so no need, burden, or breakthrough is carried alone.
We gather every week for Wednesday Prayer at 6:30 PM, coming together to worship, intercede, and seek God’s direction for our families, our community, and the ministry of the church. In addition, we hold monthly prayer gatherings and schedule prayer and fasting days as needed—responding to special requests, urgent needs, seasons of decision, and times of spiritual renewal.
Our Prayer Group helps organize prayer topics, communicate requests, and mobilize believers to pray with unity, faith, and compassion. If you desire to grow deeper in prayer and stand in the gap for others, you are warmly invited to join us as we pursue God together.
የጸሎት ቡድን
ጸሎት የቤተክርስቲያናችን የልብ ትርታ ነው። ጸሎት መላውን ምዕመን የሚያካትት ቢሆንም፣ የቤተክርስቲያናችንን አጠቃላይ የጸሎት ፕሮግራሞችን የሚያስተባብርና የሚያጠናክር የተለየ የጸሎት ቡድን ኣለን።
በየሳምንቱ ረቡዕ ከምሽቱ (6:30 PM) ላይ አብረን ለማምለክ፣ ምልጃን ለማቅረብ እንዲሁም ለቤተሰቦቻችን፣ ለማኅበረሰባችንና ለቤተክርስቲያናችን አገልግሎት የእግዚአብሔርን አመራር ለመጠየቅ እንሰበሰባለን። በተጨማሪም በየወሩ የጸሎት ስብሰባዎችን እናደርጋለን፤ እንደ አስፈላጊነቱም ለልዩ ልዩ ጥያቄዎች፣ ለአስቸኳይ ፍላጎቶች፣ ለውሳኔ ወቅቶችና ለመንፈሳዊ ተሃድሶ የጸሎትና የጾም ቀናትን እንመድባለን።
የጸሎት ቡድናችን የጸሎት ርዕሶችን በማደራጀት፣ ጥያቄዎችን ለምዕመኑ በማድረስና አማኞች በአንድነት፣ በእምነትና በርኅራኄ እንዲጸልዩ በማንቀሳቀስ ረገድ ትልቅ ሚና ይጫወታል። በጸሎት ሕይወታቸዉ እንድበረቱና እንዲያድጉ ምዕመናንን ያነሳሳሉ። እርስዎም ለመማለድና ለመጸለይ ፍላጎት ካለዎት፣ አብረን የእግዚአብሔርን ፊት እንድንፈልግ በደስታ እንጋብዞዎታለን።