The Maryland Kale Heywet Church exists to proclaim Christ, disciple believers, plant churches, and empower communities through Gospel-rooted teaching, loving fellowship, and spiritual growth. We envision a vibrant, Christ-centered family where faith is alive, love is active, and hope is contagious — a community transformed by the power of the Gospel and dedicated to renewing lives and shaping generations. Our heart is to see individuals changed, families strengthened, and communities restored through the truth of God’s Word — building a lasting legacy of disciples who make disciples, shining His light across cultures and nations. “You are the light of the world. A city on a hill cannot be hidden.” — Matthew 5:14
ራዕያችን
የሜሪላንድ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን የመኖር ዓላማዋ ክርስቶስን መስበክ፣ አማኞችን ማነጽ (ደቀ መዛሙርት ማድረግ)፣ አብያተ ክርስቲያናትን መትከል፣ እና በወንጌል ላይ በተመሠረተ ጤናማ ትምህርት፣ በፍቅርና በሕብረትና በመንፈሳዊ እድገት ማህበረሰቡን ለማብቃት ነው።
እምነት ሕያው የሆነባት፣ ፍቅር የሚሠራባት፣ እና ተስፋ የሚታይባት ንቁና ክርስቶስን ማዕከል ያደረገች ቤተሰብ ለመሆን እንመኛለን — በወንጌል ኃይል የተለወጠ፣ ሕይወትን ለማደስና ትውልድን ለመቅረጽ የተጋ ማህበረሰብ። ልባዊ ምኞታችን በእግዚአብሔር ቃል እውነት ግለሰቦች ሲለወጡ፣ ቤተሰቦች ሲጠነክሩ፣ እና ማህበረሰቦች ሲታደሱ ማየት ነው — ይህም ደቀ መዛሙርትን የሚያፈሩ ደቀ መዛሙርትን በማፍራት፣ ብርሃኑን በባህሎችና በሕዝቦች ሁሉ መካከል በማብራት ዘላቂ ቅርስን መገንባት ነው።
“እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ፤ በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አትችልም።” — ማቴዎስ 5:14
The Maryland Kale Heywet Church exists to glorify God by:
Our mission flows from Christ’s Great Commission — to “go and make disciples of all nations” (Matthew 28:19). We are called to live by faith, to walk in love, and to labor together for His Kingdom.
ተልዕኮኣችን
የሜሪላንድ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን የመኖር ዓላማ እግዚአብሔርን በሚከተሉት መንገዶች ለማክበር ነው፦
ተልዕኳችን የሚመነጨው “ሂዱና አሕዛብን ሁሉ ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው” (ማቴዎስ 28:19) ከሚለው የክርስቶስ ታላቅ ተልዕኮ ነው። የተጠራነው በእምነት ለመኖር፣ በፍቅር ለመመላለስ እና ስለ መንግሥቱ አብረን ለመድከም ነው።
Our Commitment
We are committed to being a Christ-centered, Spirit-led, and mission-driven church community that lives out its faith both inside and outside the walls of the church. We believe that every believer is called to be a light — in their family, workplace, and neighborhood. Through worship, discipleship, and fellowship, we aim to raise a generation that carries the truth of Christ wherever they go.
ቁርጠኝነታችን
እኛ ከቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢና በውጭም ሆነ በውስጥ እምነታችንን በተግባር የምንገልጥ፤ በክርስቶስ ላይ ያተኮርን፣ በመንፈስ የምንመራ እና በተልእኮ ላይ የተመሠረትን የቤተክርስቲያን ማኅበረሰብ ለመሆን ቆርጠን ተነስተናል። እያንዳንዱ አማኝ በቤተሰቡ፣ በሥራ ቦታው እና በአካባቢው ብርሃን እንዲሆን ተጠርቷል ብለን እናምናለን። በዝማሬ (በአምልኮ)፣ በደቀ መዝሙርነት እና በኅብረት አማካኝነት፤ በሄዱበት ሁሉ የክርስቶስን እውነት የሚሸከም ትውልድን ለማፍራት ዓላማ አለን።
Our Core Values
Our values reflect who we are and what we live for — they are the heartbeat of our ministry and the foundation of our mission.
Rooted in Scripture and modeled after Christ, we seek to live these values daily in our worship, our fellowship, and our service.
መሠረታዊ እሴቶቻችን
እሴቶቻችን ማንነታችንን እና የምንኖርለትን ዓላማ ያንጸባርቃሉ — እነርሱ የአገልግሎታችን የልብ ትርታ እና የተልዕኳችን መሠረት ናቸው። በቅዱሳት መጻሕፍት ላይ ተመሥርተን እና የክርስቶስን ምሳሌነት ተከትለን፣ እነዚህን እሴቶች በየዕለቱ በአምልኮኣችን፣ በሕብረታችን እና በአገልግሎታችን ለመኖር እንተጋለን።