Join Us Live in Worship
Welcome to the live stream ministry of Maryland Kaleheywet Church. We are grateful to connect with you through Facebook, Zoom, and YouTube as we worship God together in prayer, praise, and the preaching of His Word. Our desire is to reach hearts, strengthen faith, and share the love and truth of Jesus Christ with everyone near and far.
Whether you are joining from home, traveling, or unable to attend in person, you are warmly invited to be part of our worship services online. We pray that through these live broadcasts you will be encouraged, spiritually refreshed, and drawn closer to God. Join us and stay connected with our church family as we grow together in faith and fellowship.
በቀጥታ ስርጭታችን ከእኛ ጋር በአምልኮ ይቀላቀሉ
ወደ ሜሪላንድ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን የቀጥታ ስርጭት አገልግሎት እንኳን በደህና መጡ። በፌስቡክ፣ ዙም እና ዩትዩብ አማካኝነት በጸሎት፣ በምስጋናና በእግዚአብሔር ቃል ስብከት አብረን እግዚአብሔርን ስናመልክ ከእርስዎ ጋር መገናኘታችን ታላቅ ደስታችን ነው። ምኞታችን ልቦችን መድረስ፣ እምነትን ማጠናከር፣ እንዲሁም የኢየሱስ ክርስቶስን ፍቅርና እውነት በሩቅና በቅርብ ላሉት ሁሉ ማካፈል ነው።
በቤትዎ ሆነው፣ በጉዞ ላይ ሆነው፣ ወይም በአካል መገኘት ባይችሉም እንኳን፣ በመስመር ላይ ከእኛ ጋር በአምልኮ እንዲቀላቀሉ በፍቅር እንጋብዛለን። በእነዚህ የቀጥታ ስርጭቶች አማካኝነት እንድትበረታቱ፣ በመንፈሳዊ ሕይወታችሁ እንድትታደሱ፣ እንዲሁም ወደ እግዚአብሔር ይበልጥ እንድትቀርቡ እንጸልያለን። ከእኛ ጋር አብረዉ በማምለክ፤ በእምነትና በኅብረት እያደግን ከቤተ ክርስቲያናችን ቤተሰብ ጋር አብረዉ የበረከቱ ተካፋይ ይሁኑ።