Our Deacons’ Ministry serves as a steady, faithful support to the spiritual and practical life of the church. This dedicated team helps ensure that our worship gatherings are carried out with reverence, order, and care—so the congregation can focus on honoring the Lord together.
Deacons assist with key church responsibilities such as preparing and serving the Lord’s Supper, collecting tithes and offerings with integrity, and supporting church services and special events as needed. Beyond their visible service, the deacons also cultivate a strong spiritual foundation through their own weekly prayer gatherings and teaching times, growing together in humility, unity, and commitment to Christ.
If you have a heart to serve with faithfulness, compassion, and accountability, we thank God for the vital role deacons play in building a healthy and caring church family.
የዲያቆናት አገልግሎት
የዲያቆናት አገልግሎት ለቤተክርስቲያናችን መንፈሳዊና ተግባራዊ ሕይወት አስፈላጊና ደጋፊ በመሆን ያገለግላል። ይህ ለአገልግሎቱ የተሰጠ ቡድን የአምልኮ መርሃ-ግብሮቻችንን በክብር፣ በሥርዓትና በጥንቃቄ እንዲከናወን በማድረግ፤ ምዕመኑ በሙሉ ልቡ ጌታን በማክበር በማምለክ ላይ ብቻ እንዲያተኩር የሚያገለግሉ ናቸዉ።
ዲያቆናት እንደ ጌታ እራት ዝግጅትና ሥነ-ሥርዓት፣ አስራትንና መባን በታማኝነት መሰብሰብ፣ እንዲሁም እንደ አስፈላጊነቱ ለቤተክርስቲያን አገልግሎቶችና ለልዩ ሁነቶች ድጋፍ በመስጠት ረገድ ቁልፍ ኃላፊነቶችን ይወጣሉ። ከሚታየው አገልግሎታቸው ባሻገር፣ ዲያቆናቱ በየሳምንቱ ለጸሎትና ለትምህርት ጊዜ በመዉሰድ ጠንካራ የራሳቸዉን የማጠናከሪያ ፕሮግራም ኣላቸዉ፤ በዚህም በትሕትና፣ በአንድነትና ለክርስቶስ ባላቸው ታማኝነት አብረው ያድጋሉ።
በታማኝነት፣ በርኅራኄና በኃላፊነት ስሜት የማገልገል ልብ ካለዎት፤ ጤናማ የቤተክርስቲያን ቤተሰብን በመገንባት ረገድ ዲያቆናት ለሚጫወቱት ወሳኝ ሚና እግዚአብሔርን እናመሰግናለን።