We grow best in circles, not rows. Our Small Groups & Bible Studies meet weekly in welcoming groups of 3–7 people, organized by neighborhood and schedule convenience. Some groups gather face-to-face, others meet via Zoom or teleconference, and many offer a hybrid option so everyone can participate. Each week, our pastors prepare clear, Bible-centered study guides—either walking through books of the Bible or addressing relevant, real-life topics. These materials are distributed to every group leader, ensuring we’re learning together across the church while still enjoying the warmth of close community. With central coordination and caring leaders, our groups provide a place to study Scripture, ask questions, pray, and support one another through every season of life.
የቤት ለቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ቡድኖች
“ዕድገታችን የሚያምረው በረድፍ ስንቆም ሳይሆን በክብ ተሰባስበን ስንመካከር ነው።”
የእኛ የቤት ለቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መርሃ-ግብር፤ ከ3 እስከ 7 የሚደርሱ አባላትን በማቀፍ በየሳምንቱ ይካሄዳል። ቡድኖቹ የተዋቀሩት ለሚኖሩበት ሰፈር ቅርብ በሆነና ጊዜዉ አመቺ በሆነ መልኩ ነው። አንዳንድ ቡድኖች በአካል ተገናኝተው ሲወያዩ፣ ሌሎች ደግሞ በዙም (Zoom) ወይም በስልክ ጥሪ ይገናኛሉ፤ እንዲሁም ሁሉም እንደ ምርጫው እንዲሳተፍ በሁለቱም መንገድ (በአካልና በኢንተርኔት) የሚያካሄዱ አሉ።
በየጊዜዉ ፓስተሮቻችን የመጽሐፍ ቅዱስን መጻሕፍት መሠረት ያደረጉ ወይም ወቅታዊ የሕይወት ጉዳዮችን የሚዳስሱ ግልጽ የጥናት መመሪያዎችን ለሁሉም ቡድኖች በወጥነት ያዘጋጃሉ። እነዚህ የጥናት ቁሳቁሶችና ትምህርቶች ለሁሉም የቡድን መሪዎች የሚሰራጩ ሲሆን፣ ይህም መቀራረብን ፣ ፍቅርንና በአንድነት መማርን ከማጎልበቱም በላይ በመላዉ ቤተክርስቲያናችን ምዕመናን ዘንድ ተመሳሳይ መንፈሳዊ ግንዛቤ እንዲኖረን ይረዳል። ቡድኖቻችን ቅዱሳት መጻሕፍትን የምናጠናበት፣ ጥያቄዎችን የምንጠይቅበት፣ የምንጸልይበትና በማንኛውም የሕይወት ውጣ ውረድ ውስጥ እርስ በርሳችን የምንደጋገፍበት ሞቅ ያለ የግኑኝነት ስፍራ ናቸው።