Our church is passionate about raising the next generation with strong faith and a joyful love for Jesus. Each week we provide age-appropriate, Bible-centered programs for Children, Youth, and Young Adults—designed to meet each group where they are and help them grow.
We are currently seeking gifted, dedicated teachers and mentors—especially native English speakers—who have a heart to serve and disciple children and young adults. If you feel called to invest in the next generation, we would love to welcome you to this ministry. Come join us as we teach, encourage, and build a lasting foundation of faith—week after week.
የሕፃናት፣ የወጣቶች እና የጎልማሶች አገልግሎት
ቤተክርስቲያናችን ቀጣዩ ትውልድ በጠንካራ እምነትና ለኢየሱስ ባለው ደስ የሚል ፍቅር እንዲያድግ ከፍተኛ ፍላጎትና ራእይ አላት። በየሳምንቱ ለሕፃናት፣ ለታዳጊ ወጣቶችና ለወጣቶች እንደ እድሜያቸው የተዘጋጁ፣ መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት ያደረጉ መርሃ-ግብሮችን እናቀርባለን። እነዚህም ፕሮግራሞች እያንዳንዱን የዕድሜ ክልል ባሉበት ደረጃ የሚያገኙና እንዲያድጉ የሚረዱ ናቸው።
በአሁኑ ወቅት፣ ሕፃናትንና ወጣቶችን የማገልገልና በደቀ መዝሙርነት የማሳደግ ፍላጎት ያላችሁ፣ ተሰጥኦ ኣለኝ የሚትሉ መምህራንና አገልጋዮችን (በተለይም የእንግሊዝኛ ቋንቋ ተናጋሪ የሆኑ) ስለምንፈልግ መሪዎችን እንድታነጋግሩ እንጠይቃለን። በሚቀጥለው ትውልድ ላይ አሻራዎን ለማሳረፍ ጥሪው ካለዎት፣ ወደዚህ አገልግሎት በደስታ እንቀበልዎታለን። በየሳምንቱ እያስተማርን፣ እያበረታታንና ዘላቂ የሆነ የእምነት መሠረት እየገነባን አብረውን ያገልግሉ።